“ባዕድ ይዛመድ!” – ሲል ታላቁ ባለቅኔ


Ben Ephrem | 23 September 2016 በዘመድ ስም ከሚሸምተው ነጋዴ (ስሙን አጎት፤ አክስት፤ እህት፤ ወንድም፤ እናት ጅኒ ቁልቋል…ብሎ ከምግባሩ በላይ ከቆለለው ‹‹የዝምድና ቢዝነስ- ማን›› ይሰውራችሁ ሲል ነው:: በጥልቀት ህይወት ሲጤን— ከብቻነትና ከብቸኝነት ምጥ ውስጥ ያፈሰስክለትን ውለታዎች (ልክ የነጠረ ክፋቱን/ቷን እንደማታውቅ ሁላ) ዛሬም እንደጅልነት እየቆጠረ አጉል ብልጥ ሲሆን(ትንሽ ሲራመድ የሚደቅ ሸክላ ብልጥነት)፤ አንተም እንደ ጅል ስትሰማው እና— ሲኮፈስ አንድ አፍሪቃዊ የሚኖረውን ሙሉ ዕድሜ የፈጀ ቢዝነስ ማንን … Continue reading “ባዕድ ይዛመድ!” – ሲል ታላቁ ባለቅኔ

ሄሊ እና የመንዝ ወርቅ


በህይወት እምሻው በዚያ ሰሞን ለአጭር ጊዜ ስራ የተቀጠርኩበት አንድ ቢሮ ፈረንጅ አለቃዬን ልተዋወቃት ቢሮዋ ሄድኩ፡፡ ‹‹ኦው!አዲሷ ኮንሰልታንት! ማነው ስምሽ?›› አለችኝ አየት አድርጋኝ፡፡ ‹‹ሕይወት እምሻው›› እኔን ሳይሆን የምታገላብጠውን የወረቀት ክምር አያየች ‹‹ኦህ…አጠር አድርጊውና ንገሪኝ ›› አለችኝ ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ‹‹ይቅርታ ምን አልሽኝ?›› አልኳት :: ‹‹እዚህ ሀገር ስማችሁ ረጅም ነው…አይያዝም..አጠር አርገሽ ንገሪኝ እስቲ›› ደሜ ሲግል ተሰማኝ፡፡ ይሄ እኮ የሕይወት ታሪክ ወይ ወርሃዊ ሪፖርት አይደለም፡፡ ስም እንዴት ነው … Continue reading ሄሊ እና የመንዝ ወርቅ

ደም ባላስለቅስሽ ወንድ አይደለሁም


በሠናይት ንዋይ እንዲህ እንደሳቅሽ ደም ባለስለቅስሽ ወንድ አይደለሁም/ማስለቀስ የፆታ ማረጋጋጫነትን ያጎናፅፍ ይመስል/የሚል ወገብ የሚያስነቀነንቅ ፉከራ የሰማሁት ጠዋት ከቤቴ ወደ ዋነኛው አስፋልት የምትወስደውን ቀጭን አስፋልት ይዤ በመጓዝ ላይ እያለሁ ነበር፡፡ ለወትሮው ይሄ መንገድ የተጠበሰና የተቀቀለ በቆሎ፣ጎመን ሽነኩርትና ቲማቲም በሚሸጡ ጎስቋላ ሴቶች ተጣቦ ይታያል፡፡ያለከልካይ ከገበያተኛው ጋር ሲለዋወጡ አርፍደው ያመሻሉ…….. ዛሬ ታዲያ ባልተለመደ ሁኔታ ገና የሐምሌ ፀሀይ ለተመፅዋቾቿ ሙቀቷን በአግባቡ ሳትለግስ እነዚህን የመንገድ ዳር ልማታዊ ባለጉልቶች /ልማታዊ ነጋዴ … Continue reading ደም ባላስለቅስሽ ወንድ አይደለሁም

ለሠዎች የሚፈልጉትን ስጣቸው


በሠናይት ንዋይ የጥናት ባለሙያ ነኝ …… አዲሱ ጥናቴ የሚያተኩረው በአንድ ጎሰቋላ መንደር ማህበረሰብ የአኗኗር ሁኔታ ላይ ነው……… የዚህን ማህበረስብ የኑሮ ሁኔታ በቦታው ተገኝቼ ማጥናት ነበረብኝና ወደ ቦታው ተጉዤ ከባላገሩ ጋር እየኖርኩ ….አሹቁን አብሬ እየቃምኩ….. ጉሽ ጠላውን አብሬ እየተጎነጨሁ ….. የሽንብራውን እሸት አብሬ እየጠረጠርኩ …… ብስል ከጥሬ አብሬ እየተቋደስኩ /በቸም ባላገር ደግ ነው/ኖሮውን ሁሉ አብሬ እየኖርኩ ጥናቴን አካሄድኩ፡፡ከወራት በኋላ ጥናቱ ሲጠናቀቅ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ይሄ ማህበረሰብ … Continue reading ለሠዎች የሚፈልጉትን ስጣቸው

ሀገሬ


አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት። አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ። አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ። ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም። አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት። እዚያ አለ ነጻነት። በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣ እዚያ አለ ነጻነት። አገሬ ሃብት ነው። ጎመኑ ስብ ጮማ፣ … Continue reading ሀገሬ

የት አባቱ ሞትም ይሙት


እባካችሁ ዘመዶቼ፣ ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት በሳቅ በደስታ ግደሉት በሃሴት በዕልልታ ውገሩት፤ እባካችሁ ዘመዶቼ፣ ለሞት የልብ ልብ አትስጡት ናቁት አጥላሉት አውግዙት በሙሾ ግነን አትበሉት በሞቴ፣ እንዳታስደስቱት። እንደ ዶርዜ ወንድሞቼ በሳቅ ታጅቤ ኮርቼ ሞቴን በዘፈን ሞልቼ በዳንኪራ ሰበቃና፣ በዘፈን ሆይታ አካትቼ በሠርጌ ብቀበር ሞቼ እፀድቅ ነበር ባትረሱ በእንባ ውሌን ባታፈርሱ። እባካችሁ ዘመዶቼ፣ በሳቅ ጉዞ ፍታት ፍቱኝ በሙሾ ዋይታ አታጅሉኝ፤ እናቴም ፊትሽ አይክሰል በእልልታ ብርሃን ይንበልበል፤ በእረፍቴ … Continue reading የት አባቱ ሞትም ይሙት

የገብረ ክርስቶስ ደስታ አስሩ (ዘመን አይሽሬ) የፍቅር ግጥሞች!!!


የገብረ ክርስቶስ ደስታ አስሩ (ዘመን አይሽሬ) የፍቅር ግጥሞች!!! ከአንዷለም ክብረት  የመጀመሪያ ቀን አየችው ተያዩ አየና ወደዳት ቀኑ ማታ ነበር ወደ ሆቴል ሄዱ ሁለት እራት መጣ ብርጭቆው ተጋጨ አየችው ተያዩ አያት ተሳሳቁ በጠረጴዛው ስር ጭኗ ጭኑን ነካው አየችው ፈገገ እጇን በእጁ ያዘው ጠበቅ አደረጋት ጠበቅ አረገችው ከፈሉና ወጡ በከሰለው ሌሊት ሁለቱ ነደዱ ታፋቸው ጋለ ቤቱ ተቃጠለ ፍራሹ ነደደ ፍቅር ተያያዘ፡፡ ያገረሸ ፍቅር የሰማይ አሞራ ላዋይህ ችግሬን … Continue reading የገብረ ክርስቶስ ደስታ አስሩ (ዘመን አይሽሬ) የፍቅር ግጥሞች!!!

አማርኛ


እንግሊዘኛ ፡ ሲባል ፡ ቀድመው ፡ በአይኔ ፡ ላይ ፡ የሚዞሩት ፡ ሞላ ፡ ያለ ፡ ጉንጭ ፡ ያላት ፡ ንግስት ፡ ቪክቶሪያ ፡ እና ፡ ንግስት ፡ ኤልሳቤት ፡ ናቸው፡፡ ሁለቱ ፡ ሊቃነ ፡ መናብርት ፡ በሀገራችን ፡ የሴቶች ፡ መብት ፡ ከወንዶች ፡ እኩል ፡ እዲከበር ፡ በቀጥታም ፡ ባይሆን ፡ በተዘዋዋሪ ጉልህ ፡ አስተዋእፆ ፡ አበርክተዋል፡፡ ለሰው ልጅ ተግባራዊ ክዋኔ የሐሳብ መነሻው … Continue reading አማርኛ

ፍቅር ያስተፈስህ ልበ ሰብ!


ንጉስ! በተንጣለለው ‘ርስቴ የከበርኩ፣ ፍሰሀ’ን ለብሼ ሀሴትን የደረብኩ፣ ውስጤ የማይቆረቁረኝ የተመቻመችኩ፣ የሠላ ጎራዴ በአፎቴ ያኖርኩ፤ ለታዘዙኝ የጨርቅ መንገድ አስነጣፊ፣ ላስቆጡኝ ሺህ ጦር አዝምቼ ተናዳፊ፤ የራሴ አዛዥ፣ የራሴ ገዥ፤ “ንጉስ የከበርኩ!” እነግርሻለሁ… ፍቅር ሲይዝ ዘላለም ቅርብ ነው፣ ዙፋንም መቀመጫ ብቻ ነው፣ ማን “አለው!” ባይ ይሆን የሚመክተው? ባህል? ርቀት? ክብር? ቅርበት? ዝና? ርስት? ሠይፍ? ወቅት? የትኛውን ፈርቶ ይሆን፣ “አንተስ በፀበልህ!” የሚል? እነግርሻለሁ… በመልካምነትሽ ጠብታ ዘር፣ ከአይኔ ያሉትን … Continue reading ፍቅር ያስተፈስህ ልበ ሰብ!