‹‹አእምሮን በተገደበ ነፃነት ውስጥ ማንቀሳቀስ ትርፉ ባርነት ነው››


‹‹ጉንጉን›› እንዲሁም ‹‹የወዲያነሽ›› በተሰኙ መጻሕፍቱ ይታወቃል፤ ኃይለመለኮት መዋዕል። እርሱ ዋናው ሥራዬ መምህርነት ነው፤ ደስታና ክብር የሚሰማኝ በመምህርነቴ ስጠራ ነው ቢልም፤ እነዚህ መጻሕፈቱ ዘመን ተሸጋሪ ደራሲ አሰኝተውታል። ሰሜን ሸዋ ማጀቴ ከተማ 1943 ነው ትውልዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ወሎ ኮምቦልቻ የተማረ ሲሆን፣ ከ5ኛ ክፍል እስከ 8ኛ አስመራ አክሪያ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። ኹለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ ልዑል መኮንን ትምህርት ቤት ተምሯል። 1962 ጀምሮ በመምህርነት ማገልገል የጀመረው ኃይለመለኮት፣ ከ1969 ጀምሮ እስከ 1972 በእስር ቆይቷል። ‹‹በእኔ እምነት ዋናው ሥራዬ መምህርነት ነው።›› የሚለው ኃይለመለኮት፣ ከ43 ዓመታት በላይ በመምህርነት ሠርቷል። አሁንም ላይ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመሆን በተለያዩ ክልል ከተሞችና ትምህርት ቤቶች እየተንቀሳቀሰ የንባብን ባህል በተመለከተ እይታውን፣ ልምዱንና እውቀቱ ያካፍላል። የንባብን ነገር በሚመለከት እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ስምምነትን ተከትሎ ከ50 ዓመት በኋላ ኤርትራ የሔደበትን ምክንያትና ሌሎችም ጉዳዮችን በማንሳት ከአዲስ ማለዳዋ ሊድያ ተስፋዬ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል።

Blog at WordPress.com.

Up ↑